Fana: At a Speed of Life!

መጪው ዘመን ብሩህ ነው -ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መጪው ዘመን ብሩህ ነው ፤ የምንሸጋገርበት እና የማንቻል መሆናችንንም የምናረጋግጥበት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም የጀመርናቸው ስራዎች ሁሉም ባስቀመጥነው እቅድ መሰረት እየተጠናቀቁ የኢትዮጵያን መጽናት እና መላቅ እንደሚያረጋግጡ የአረንጓዴ አሻራ ማሳያ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ገናናነት እና ነጻነት የሚረጋጠው ደግሞ መላው ህዝብ በሁሉም ግንባር በአንድ ልብ ሲቆም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ኢትዮጵያ የገጠማትን ጦርነት እናሸንፋለን ፤ሰላም እናመጣለን፤ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትንም እናረጋግጣለን ብለዋል።

ኢትዮጵያ በአራት አመታት ውስጥ 20 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል አቅዳ በ2011 በጀመረችው ስራ አሁን ላይ 18 ቢሊየን ችግኝ ተክላለች።

በአልዓዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.