Fana: At a Speed of Life!

የአካባቢው መልክአ ምድር ያልበገረው ሠራዊት ከፍተኛ ድል አስመዝግቧል – የማይጠብሪ ግንባር የጦር አዛዦች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በማይጠብሪ ግንባር የገባው የአሸባሪው ትህነግ ቡድን በወቅን በኩል አድርጎ ደባርቅና ዳባትን ለመቆጣጠር ቢያስብም ሳይሳካለት ቀርቷል።

በቀጠናው ለአምስት ተከታታይ ቀናት የኢትዮጵያ ጥምር ጦር ባካሄደው ውጊያ ጠላት አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ተመልሷል።

የጦር አዛዦቹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ወቅታዊ የአየር ሁኔታና የአካባቢው መልክአ ምድር ያልበገረው ሠራዊት በርካታ የጠላት መሳሪያዎችን ከከባድ እስከ ቀላል ማርኳል።

በዚህ ግንባር ለተገኘው ድል የሰሜን ጎንደር ህዝብ ከሁሉም የፀጥታ ሀይል ጋር የነበረው ትብብርና ድጋፍ የሚመሰገን ነው ያሉት አዛዦቹ በቀጣይም ይህንን ኢትዮጵያዊ ወኔና አንድነት በማስቀጠል አሸባሪውን ቡድን እስከመጨረሻዉ ማስወገድ ይገባል ብለዋል።

በሙሉጌታ ደሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.