Fana: At a Speed of Life!

ወደ አማራ ክልል የገባ ጠላት ተመልሶ አይወጣም – የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ አማራ ክልል የገባ ጠላት ተመልሶ አይወጣም ሲሉ የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያለአለም ፈንታሁን ተናገሩ።

አቶ ያለአለም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት መግለጫ የትህነግ ቡድን ወረራ ማካሄድ እንደጀመረ ሁሉም የፀጥታ መዋቅር ከህብረተሰቡ ጋር በመወያየት ጠላትን እንደገባ ለማስቀረት ባሰበው መሰረት እውን ማድረግ ተችሏል።

ከዞን እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ የሚገኘው አመራርም ግንባር ድረስ በመዝለቅ እያሳዩት ያለው ድጋፍ ድል ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ነበረው ብለዋል።

በተለያየ አቅጣጫ ወረራ ለመፈፀም ያሰበው የአሸባሪው ቡድን ህዝቡን ስጋት ውስጥ ከቶት ነበር ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ሆኖም ግን በነበረው ትብብርና የጋራ ትግል ጠላትን ደምስሶ ከአካባቢው ማስወገድ ተችሏል ብለዋል።

በቀጣይም የዞኑ ህዝብ ከሠራዊቱ ጎን በመሆን የጠላትን ፍፃሜ ለማፋጠን እንዲረባረብ ሲሉ አሳስበዋል።

በሙሉጌታ ደሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.