Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል ፖሊስ አባላት፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፀጥታ አካላት ጁንታው ይዞት የነበረውን ስትራቴጂክ ተራራ አስለቀቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በወሎ ግንባር የዘመቱት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ጁንታው ይዞት የነበረውን ስትራቴጂክ ተራራ ማስለቀቃቸው ተገለፀ ፡፡

አባላቱ በቅንጅት ያስለቀቁት ቦታ በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ በጎሀ ተራራና አካባቢ ሲሆን÷ በስፍራው መሽጎ የነበረውን የአሸባሪውን ህወሃት ጁንታ ቡድን ታጣቂዎችን ባካሄዱት እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ የጁንታው ቡድን ታጣቂዎች ላይ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራም አድርሰዋል።

በዚህም ተራራውን ሙሉ በሙሉ ማስለቀቀቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ሰሜን ዳይሬክቶሬት የዲቪዥን አራት አባሎች የገለፁ ሲሆን÷ ፀረ-ህዝቡ አሸባሪው ጁንታ ቡድን በደረሰባቸው ቦታዎች ሁሉ የህዝብና የመንግስት ሐብትና ንብረት እየዘረፈና እያቃጠለ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

የዲቪዥኑ አመራሮችና አባላት የተሰጠንን ተልዕኮና ስምሪት ተቀብለን አሸባሪው ጁንታ ቡድን እስኪጠፋ ድረስ ሌት ተቀን ያለ እረፍት በመስራትና መግቢያና መውጫ በማሳጣት የገባበት ገብተን እንደመስሰዋለን ሲሉ በአፅንኦት መናገራቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.