Fana: At a Speed of Life!

የካፋ ዞን ነዋሪዎች መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ አሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የካፋ ዞን ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍና አሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በቦንጋ ከተማ አካሄዱ፡፡

ሰልፈኞቹ አሸባሪ ቡድኖቹ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት አውግዘዋል።

የሰልፉ ተሳታፊዎች “መከላከያ ሰራዊታችን የሉዓላዊነታችን ምልክት ነው፣ ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጎን ነን፣ የህወሀት ጁንታ ቡድን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠላት ነው፣ የአብሮነት ጉዟችን በሽብርተኞች አይደናቀፍም፣ ሰላማችን በአንድነታችን ይጠበቃል፣ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የሚከፈል ዋጋ ክቡር ነው፣ ኢትዮጵያ በጀግኖቿ አፍራ አታውቀም” የሚሉ መፈክሮችን አስተጋብተዋል።

ነዋሪዎቹ ሀገርን ከጥፋት ኃይሎች ለመታደግና ለመከላከያ ሰራዊት እያደረጉት ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ እስከ መስዋአትነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ማረጋገጣቸውን ከከፋ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.