የደብረ ብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያስተማራቸውን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የደብረ ብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያስተማራቸውን 158 የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በ11 የትምህርት አይነቶች በመደበኛው እና በማታው ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 158 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ግቢ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ቴዎድሮስ ክፍለዩሀንስ ሀገራችን በአሁኑ ሰአት ባጋጠማት የህልውና ዘመቻ በርካታ ወገኖች የእናንተን ድጋፍ እና እርዳታ በሚሹበት ወቅት በመመረቃችሁ ታሪካዊ ሀላፊነት ጭምር አለባችሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን የጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ገስጥ ጥላሁን በበኩላቸው ÷ወደ ማህበረሰቡ ስትቀላቀሉ በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ የቀሰማችሁትን እውቀት በመጠቀም በሀገራችን በዘርፉ ያለዉን ችግር ለመቅረፍ የራሳችሁን አስተዋፅኦ ማበርከት ይጠበቅባችኋል ብለዋል።
ተማሪዎቹም ሀገር የእነሱን እርዳታ በምትሻበት በዚህ ሰአት በመመረቃቸዉ መደሰታቸዉን ገልፀው ሀላፊነታቸውን ለወጣት ዝግጁ ነን ብለዋል።
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!