Fana: At a Speed of Life!

በሀዲያ ዞን የሚገኙ የትምህርት ተቋማት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 18 ሰንጋዎችን ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሀዲያ ዞን የሚገኙ 15 የግልና 5 የመንግስት የትምህርት ተቋማት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 18 ሰንጋዎችን ድጋፍ ማድረጋቸዉን የዞኑ ቴክኒክና ሙያ መምሪያ አስታወቀ።

በሀገር ላይ የተደቀነዉን የህልዉና አደጋ ለመመከት በቀጣይም ለመከላከያ ሠራዊት ያላቸዉን አጋርነት እንደሚገልጹ ተቋማቱ ገልጸዋል።

የሆሳዕና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ አወል ሸንጎ እንዳሉት የኮሌጁ ማህበረሰብ አባላት በ67 ሺህ ብር የተገዙ ሁለት ሰንጋዎችን ለሰራዊቱ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ የሆሳዕና ካምፓስ ዲን አቶ ነጋ አባቦራ በበኩላቸዉ ዩኒቨርሲቲዉ የመንግስትን ጥሪ በመቀበል መላዉ ሠራተኞች የማናጅመንት አባላትና የበላይ ኃላፊዎች የጋራ ዉይይት በማድረግ ከደመወዛቸዉ በማዋጣት በ80 ሺህ ብር ሁለት ሰንጋዎችን በመግዛት ለሰራዊቱ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል።

የአትላስ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የሆሳዕና ካምፓስ ዲን አቶ ታደሰ ማቲዎስ እንዳሉት በሀገር ላይ የተደቀነዉን የህልዉና አደጋ ለመመከት በዱር በገደል ከጠላት ጋር እየተፋለመ ላለዉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኮሌጁ ባለቤት የማናጅመንት አባላትና ሠራተኞቹ 25 ሺህ ብር ወጪ በማድረግ አንድ የሰንጋ ድጋፍ ማድረጋቸዉን አስረድተዋል።

በቀጣይም እስከ ጦር ግንባር ድረስ ሄዶ ሠራዊቱን ከመቀላቀል ጀምሮ በማንኛዉም መልኩ ተቋማቱ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ስለመሆናቸዉም ኃላፊዎቹ መጠቆማቸውን ደሬቴዴ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.