Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ቡድን ለተፈናቀሉ ከ16 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ምግብና አልባሳት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሃት ቡድን ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ16 ነጥብ 7 ሚሊዮየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረገ።

የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ ወይዘሮ ሙና አህመድ ድጋፉን ለአፋር ክልል መንግስት አስረክበዋል ።

ሚኒስቴር ዴኤታዋ በወቅቱ እንዳሉት አሸባሪው ህወሃት የደቀነብንን የህልውና አደጋ ለመመከት ህዝቡ ሴት ወንድ ሳይል መስዋእትነት እየከፈለ ነው።

“የከሀዲው ቡድን ግብአተ-መሬቱ በቅርቡ ይፈጸማል” ያሉ ሲሆን የአሸባሪው አባላት በየደረሱበት ሁሉ በሴቶችና ህጻናት ላይ የአስገድዶ መድፈርና ተያያዥ ኢ-ሰብአዊ ጥቃቶችን መፈጸሙን አመልክተዋል።
ህጻናትን አስገድዶ ለጦርነት በመማገድ የዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ ወንጀል መፈጸሙን ጠቁመው ፤ሚኒስቴሩ ወንጀሉን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብና ለሰብአዊነት የቆሙ አካላት ለማድረስ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

“ዜጎች ላይ የተፈጸመን ችግር ለመቅረፍ ሁላችንም ከመንግስትና ተጎጂዎች ጎን በመቆም ከእለት ደራሽ እርዳታ እስከ ዘለቄታው የማቋቋም ስራዎችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ጋር በጋራ እናከናውናለን” ሲሉ ተናግረዋል።

የክልሉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ አይሻ ያሲን ድጋፉን ሲረከቡ እንዳሉት አሸባሪው የህወሃት ቡድን በክልሉ በከፈተው የእብሪት ጦርነት በተለይም በንጹሃን አርብቶ አደሮች ላይ ከፍተኛ ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አስከትሏል።

የክልሉ መንግስት አቅም በፈቀደ ሁሉ ለተጎጂዎች ድጋፍና እገዛ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው ከችግሩ ስፋትና ውስብስብ ባህሪ አንጻር የሌሎች ባለድርሻ አካላት እገዛ ማስፈለጉን አመልክተዋል።

መስሪያ ቤቱ ያደረገው ድጋፍ የተጎጅዎችን ችግር ለማቃለል ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው፤ ድጋፉ ለሌሎችም አስተማሪ የሚሆን በጎ ተግባር መሆኑን ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.