አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአሰላ ከተማ ከ84 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባውን ህንጻ መረቁ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ልዑክ በአሰላ ከተማ ከ 84 ሚሊየን ብር በላይ የተገነባውን አዲስ የአርሲ ዞን አስተዳደር ህንጻ መርቀዋል፡፡
በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ህንጻው የ 5 ሴክተር መስሪያቤቶችን ጨምሮ ቤተመጻህፈት፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የአይሲቲ ማዕከል ያለው መሆኑ ተመላክቷል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!