Fana: At a Speed of Life!

የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በብርሸለቆ ለምልምል ሰልጣኞች የመድረክ ስራዎችን አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ ቴአትር ቤቶች  የተውጣጡ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ34ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞች የመድረክ ስራዎችን አቀረቡ።

የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ጌታቸው አሊ፥ ከአራቱም የሃገሪቱ ማዕዘናት ቀፎው እንደተነካበት ንብ ሆ ብሎ ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል የተመመውን ወጣት ልታበረታቱ፣ ልታዝናኑ እና ሃገራዊ ፍቅሩን ይበልጥ ልታጎለብቱ በመካከላችን ስለተገኛችሁ ታላቅ አክብሮት ይገባችኋል ሲሉ ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አርቲስት ትዕዛዙ ታዬ እና አርቲስት አስቴር አለማየሁ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት፥ “ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት የተደቀነባትን አደጋ ለመቀልበስ ሁሉም ዜጋ በጋራ በመሆን ሃገርን የማዳን ስራ እየሰራ ስለሆነ እኛም በሞያችን ካለበት ድረስ በመሄድ ኑሮውን፣ ደሙን እና ህይወቱን ለሃገሩ ለሰጠው ለመከላከያ ሰራዊት የኪነ-ጥበብ ስራ በማቅረባችን ታላቅ ኩራት ይሰማናል” ብለዋል።

የኪነጥበብ ባለሙያዎቹ ከሃገር ፍቅር ቴአትር፣ ራስ ቴአትር፣ ህፃናት እና ወጣቶች ቴአትር እና አዲስ አበባ ቴአትር እና ባህል አዳራሽ የተውጣጡ መሆናቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.