Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሠራዊቱ የጀመረውን ሽብርተኛውን  የመደምሰስ  ስራ  አጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ  መከላከያ ሠራዊት ፣ የጀመረውን ሽብርተኛውን ጠራርጎ የመደምሰስ ስራ  አጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ ።

በዚህም ሰራዊቱ   ሰፊ የፀረ-ማጥቃት እርምጃውን አጠናክሮ ቀጥሏል ።

አሸባሪው ህወሃት የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔን እና ለትግራይ ህዝብ የተሰጠውን የጥሞና ጊዜ አሻፈረኝ በማለት በአማራና አፋር ክልል ወረራ በመፈፀም እጅግ ዘግናኝ ግፎችን ሲፈፅም ቆይቷል።

የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ  ፥ የመከላከያ ሰራዊታችን እስትራቴጂክ ቦታዎችን ይዞ በመከላከል ቁመና ራሱን ለቀጣይ ግዳጅ ሲያዘጋጅ ቆይቷል ብለዋል።

አሁን ላይ ከመከላከል ቁመና ወደ ፀረ-ማጥቃት በመሸጋገር ሽብርተኛው ወረራ ከፈፀመባቸው ቦታዎች ሁሉ ጠራርጎ ለማውጣትና ለመደምሰስ  ጀግናው ሠራዊታችን ማጥቃት መጀመሩን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.