Fana: At a Speed of Life!

ጁንታውን እስከወዲያኛው ለመቅበር ከሰራዊታችን ጎን እንሰለፋለን-የኮምቦልቻ ተመራቂ ወጣቶች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጁንታውን እስከወዲያኛው ለመቅበር ከሰራዊታችን ጎን እንሰለፋለን ሲሉ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና የወሰዱ ተመራቂ ወጣቶች ተናገሩ።

የህወሓትን ወረራ መመከት ብቻ ሳይሆን ሀገር እረፍት የምታገኘው ጁንታው ደብዛው ሲጠፋ በመሆኑ በመስዋዕነት ለሀገራችን መዳን እንሰለፋለን ብለዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሀሰን፥ ተመራቂዎቹ የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ ዝግጁ የሚያደርጋቸውን ስልጠና ከመውሰዳቸው ባሻገር የመከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል በርካቶቹ ጥሪ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ናቸው ብለዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ ዶክተር ኢንጅነር ከማል መሀመድ፥ ያሉንን ልዩነቶች ወደጎን በመተው ትግላችንን በማስተባበር ትህነግን የማጥፋት ታሪካዊ አደራ ተጥሎብናል በማለት ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው በስልጠናው የተሳተፉትን አመስግነዋል።

ለሰልጣኞቹም ቃለ መሀላና የሰንደቅ አላማ ርክክብ አድርገዋል።

በአንድነት ናሁሰናይ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.