Fana: At a Speed of Life!

የገቢዎች ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ለተፈናቀሉ ዜጎችና ለጸጥታ አካላት ከ71 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ጉምሩክ ኮሚሽን እና ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከ71 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ለተፈናቀሉ ወገኖች እና አሸባሪውን የትህነግ ቡድን እየተፋለሙ ላሉ የጸጥታ አካላት ድጋፍ አደረጉ፡፡
ተቋማቱ ያደረጉት ድጋፍ ሽብርተኛው የትህነግ ወራሪ ቡድን በፈጸመው ወረራ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች እና አሸባሪውን የትህነግ ቡድን እየተፋለሙ ላሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ የሚውል ነው ተብሏል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ፥ድጋፉን ያደረጉት መሥሪያ ቤቶች ከተጣለባቸው ኀላፊነት በተጨማሪ ሀገር ከገባችበት ችግር እንድትወጣ ሲሠሩ መቆየታቸውን ጠቁመዋል፡፡
እንደ ሀገር ያጋጠመውን ችግር ለመቅረፍ መረዳዳት እና መደጋገፍ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ድጋፉ 60 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ በዓይነት እና ቀሪው 11 ሚሊየን ብር በጥሬ መሆኑን ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ገልጸዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ፥የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ጉምሩክ ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር እያደረጉት ላለው ተከታታይ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአሸባሪው የትህነግ ቡድን ወረራ ለመቀልበስ የተቋማቱ ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ርእሰ መሥተዳድሩ “ሽብርተኛው ቡድን እየተቀበረ ነው፤ አስተሳሰቡንም በመቅበር በቅርቡ ፊታችንን ወደ ልማት እናዞራለን” ብለዋል፡፡
አሸባሪው ትህነግ ብቻ ሳይሆን የቅማንት ፅንፈኛ ተላላኪም እየተደመሰሰ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
አቶ አገኘሁ “የኢትዮጵያ ሕዝቦች የመጨረሻዋን ሳቅ ይስቃሉ፤ አሸባሪው የትህነግ ቡድን ደግሞ እስትንፋሱን ያቆማል፤ ኢትዮጵያ በልጆቿ ነፃነቷ ይረጋገጣል፤ የሽብርተኛው ቡድን የመጨረሻ መቀበሪያው በአማራ ክልል ይሆናል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
11
Engagements
Boost Post
11
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.