Fana: At a Speed of Life!

12ኛው ዙር የብስክሌተኞች እና የእግረኞች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 12ኛው ዙር የብስክሌተኞች እና የእግረኞች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሮ ውላል።
“ከጳጉሜ እስከ ጳጉሜ እንደርሳለን” በሚል መሪ ቃል በ2013 በጀት ዓመት በየወሩ ሲከበር የነበረው የመንገድ ደህንነት የንቅናቄ በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራ ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።
በዚህም በአዲስ አበባ ፣ በኦሮሚያ በሆለታ ከተማ ፣ በባህርዳር ፣ በድሬዳዋ፣ በጋምቤላ፣በሀረሪ ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተከብሯል።
መርሃ ግብሩ በእግር ጉዞ ፣ የሳይክልና በካይ ያልሆኑ የህዝብ ትራንስፖርቶችን በማስተዋወቅና የትራፊክ አደጋ እንዲቀንስ የተለያዩ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ነው መከበሩን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+4
0
People Reached
28
Engagements
Boost Post
28
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.