Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ህውሓት ላይ በሚካሄደው ዘመቻ የማህበረሰቡ ድጋፍና እገዛ የላቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህውሓት ላይ በሚካሄደው ዘመቻ የማህበረሰቡ ድጋፍና እገዛ የላቀ መሆኑን በማይጠብሪ ግንባር የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ተናገሩ።

የአካባቢው ማህበረሰብ ግንባር ድረስ በመዝመት ስንቅ በማቀበል፣ የጦር መሳሪያዎችን ከቦታ ቦታ እያንቀሳቀሰ በማገዝ ለሰራዊቱ ድጋፍ እየደረገ ይገኛል።

በማይጠብሪ ግንባር ከሁሉም አካባቢዎች ሴት ወንድ፣ ወጣት አዛውንት ሳይለይ ሰራዊቱን በማገዝ አሸባሪው እንዲደመሰስ ማህበረሰቡ የነበረው ሚና የላቀ መሆኑን አመራሮቹ ገልጸዋል።

አሸባሪው ቡድን ሰርጎ በገባባቸው ቦታዎች ሁሉ የአካባቢው ማህበረሰብ በቁርጠኝነት ተዋግቶታል ብለዋል።

ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመቀናጀትም በርካታ የአሸባሪው ቡድን ታጣቂዎች መደምሰሳቸውንና መማረካቸውን ተናግረዋል።

የአሸባሪ ቡድኑ የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶች መማረካቸውን አስታውሰው፥ በተወሰደበት እርምጃ ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታልም ብለዋል።

የትግራይን ወጣቶችን ወደ ጦርነት በመማገድ ህይወታቸውን እንዲያጡ በማድረግ በክልሉ ነዋሪ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል መፈፀሙንም ነው የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች የገለጹት።

በቀጣይ የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን ከእልቂት ለመታደግ አሸባሪውን ህወሃት ተጠያቂ ማድረግ አለባቸው  ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.