Fana: At a Speed of Life!

የሀዲያ ዞን በ3ኛ ዙር 496 የእርድ ሰንጋዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀዲያ ዞን ህዝብና አስተዳደር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለ3ኛ ጊዜ ከ47 ሚሊየን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብና በዓይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በዚህም በ3ኛ ዙር 496 የእርድ ሰንጋዎችኖ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርጓል።

በዓይነት ከተበረከተው ድጋፍ ውስጥ 496 ሰንጋ፣ 10 ፍየል፣ 10 ኩንታል ቆሎ፣ 13 ኩንታል ዳቦ ቆሎ፣ 12 ኩንታል ድርቆሽ፣ 36 ኩንታል በሶ እና 123 ኩንታል የስንዴ ዱቄት በድምሩ ከ235 ኩንታል በላይ ምግብ ይገኝበታል፡፡

ድጋፉ በዞኑ ከሚገኙ የወረዳና የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች፣ ከሀይማኖት ተቋማት፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከመንግስት ሠራተኞች እንዲሁም ከመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የተሰበሰበ መሆኑን የዞኑ የመከላከያ ሠራዊት ሀብት አሰባሰብ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ ደገፈ ታደለ ገልፀዋል፡፡

የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ በበኩላቸው፥ የዞኑ ህዝብ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚያደርገው ድጋፍ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ከዞኑ በሶስት ዙር በድምሩ ከ73 ሚሊየን ብር በላይ በገንዘብና በዓይነት ተሰብስቦ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ መደረጉን ከሀዲያ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.