Fana: At a Speed of Life!

በባሌ ጎባ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሌ ጎባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ከሦስት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የባሌ ጎባ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።
ይህ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተከማችቶ የተገኘው ከሦስት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱና በቦንዳ የታሸጉ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች የተያዙት በህብረተሰቡ ጥቆማና በከተማ ዋ ፖሊስ ጠንካራ ክትትል መሆኑን የከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር ዋና ሳጅን እንግዳ አመሃ አስታውቀዋል።
ዋና ሳጅን እንግዳ አመሃ መረጃውን ለፖሊስ ላደረሱ ግለሰቦች ፖሊስ ምስጋና አቅርበው፥ በቀጣይም የከተማው ነዋሪ ተመሳሳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ከፖሊስ ኃይሉ ጎን በመሰለፍ፣ ጥቆማ በመስጠትና መሰል ህገ-ወጥ ተግባራትን በማጋለጥ ረገድ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ማለታቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.