Fana: At a Speed of Life!

የደቡብና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በሚዛን አማን እየተገነባ ያለውን የአውሮፕላን ማረፊያ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉና የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በሚዛን አማን ከተማ እየተገነባ ያለውን የአውሮፕላን ማረፊያ ጎብኝተዋል፡፡
የአየር ማረፊያ ግንባታው ማስጀመሪያ የመሰረተ ድንጋይ ከጥቂት ወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መቀመጡ ይታወሳል፡፡
የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሳምሶን በላቸው ፥ ለግንባታው የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች ተደርገው አሁን ላይ ወደ ግንባታ መገባቱን ተናግረዋል፡፡
ለግንባታው ወደ አንድ ቢሊየን የሚጠጋ በጀት የተያዘ ሲሆን፥ 2 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር መንደርደሪያ ይሰራል ብለዋል፡፡
በዚሁ ወቅትየደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ፥የፕሮጀክቱ ግንባታ በቶሎ መጀመሩ አበረታች መሆኑን አንስተው ፥በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ትብብር ያደርጋል ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ከተጠናቀቀ የአካባቢውን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ለማጎልበት ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም አመልክተዋል፡፡
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በበኩላቸው፥ በግንባታው መጀመር ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረው የጋምቤላ ክልል መንግሥትና ህዝብ ሁለንተናዊ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
በጋምቤላ ክልል ለግንባታ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በስፋት ስለሚገኙ መጠቀም እንደሚቻለም ተናግረዋል ሲል ደሬቴድ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
95
Engagements
Boost Post
90
5 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.