Fana: At a Speed of Life!

ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድ 9ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድ ለአገራቸው በጎ ተግባር በማከናወናቸው የ2013 የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆነው ተመረጠዋል።

ፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲቋቋም ያደረጉ ኢትዮጵያዊ ናቸው።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ሲካሄድ የቆየው 9ኛው የዓመቱ የበጎ ሰው ሽልማት ለአገራቸው በጎ ስራን የሰሩና ለሌሎች አርዓያ ሊሆኑ የሚችሉ ተግባር ያከናወኑ 10 ኢትዮጵያዊያንን የሸለመው የዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማት መጠናቀቁን ኢዜአ ዘግቧል።

ለዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማት በአስር ዘርፎች ከ500 በላይ ዕጩዎች የተጠቆሙ በመርሃ ግብሩ ላይ የተጠቀሰ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥም 30 ሰዎች የመጨረሻ ዕጩ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው ተገልጿል።

ዛሬ በተካሄደው የሽልማት መርሃ ግብርም በአስር ዘርፎች ለመጨረሻ ዕጩ ከቀረቡት ሶስት ሶስት ዕጩዎች ውስጥ የመጨረሻ አሸናፊዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህ መሰረትም በመምህርነት ዘርፍ – ዶክተር ልዑልሰገድ አለማየሁ፣ በበጎ አድራጎት ዘርፍ –  አቶ አማረ አስፋው፣ በቅርስና ባህል ጥበቃ ዘርፍ – ቢላል ሃበሽ የማህበረሰብ ሙዚየም ማዕከል፣ በሳይንስ ዘርፍ – ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራ፣  በማህበራዊ ጥናት ዘርፍ – ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ፣  መንግስታዊ የስራ  ኃላፊነትን በብቃት መወጣት ዘርፍ – ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ፣  ንግድና ስራ ፈጠራ ዘርፍ – አቶ በላይነህ ክንዴ፣ በሚዲያና ጋዜጠኝነት ዘርፍ – ዶክተር ንጉሴ ተፈራ፣ በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ደራሲና ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም እና ለኢትዮጵያ ዕድገት አስተዋፅዖ ያበረቱ ዳያስፖራዎች ዘርፍ ደግሞ አቶ ኤሊያስ ወንድሙ አሸናፊ ሆነዋል።

የበጎ ሰው ሽልማት ዋና አላማ በኢትዮጵያ በጎ የሰሩ እና ለሌሎች አረአያ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ማበረታታት እና እውቅና መስጠት ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.