Fana: At a Speed of Life!

የማህበረሰቡ ድጋፍ በጁንታው ላይ እየተመዘገበ ላለው ድል የራሱ ድርሻ አለው – ሜ/ጄ መሃመድ ተሠማ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወሎ ግንባር ለሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት በደሴ ከተማ የሚገኙ በሆቴል ቱሪዝም ዘርፍ የተሠማሩ ባለሀብቶች ለሠራዊቱ ግንባር ድረሥ በማቅናት ስንቅ አቅርበዋል።

የመከላከያ ሠራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሃመድ ተሠማ እንደተናገሩት የጠላት ሀይል አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ ነው÷ ይህም በኢትዮጵያ ህዝብ ብርታት እና ወኔ ነው ብለዋል።

ጁንታው ፍርክስክሱ እየወጣ መሆኑን ያነሱት ሜጀር ጄኔራል መሃመድ በቅርብ ቀን የድል ብስራት ዜና እንሠማለን ብለዋል።

ግንባር ድረስ በመገኘት ስለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ማህበረሰረቡም ከሀሰተኛ መረጃ አስተላላፊዎች እራሡን መጠበቅ እና ከትክክለኛ የወሬ ምንጮች የተጣራ መረጃ መውሰድ አለበትም ነው ያሉት፡፡

በእሸቱ ወልደሚካኤል

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.