Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ ባሕር ዳር ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል በአሸባሪው የትህነግ ኃይል ወረራ ለተፈጸመበት የአማራ ሕዝብ ያለውን አጋርነት ለመግለጽ ርእሰ መሥተዳድሩ ባሕር ዳር ገብተዋል፡፡

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሲዳማ ክልል አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኃይልን እየተፋለመ ላለው የወገን ሠራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል 40 የበሬ ሰንጋዎችን ጨምሮ የምግብና የመጠጥ ግብዓቶችን ድጋፍ አድርጓል።

በቀጣይም አሸባሪ ኃይሉ እስከሚደመሰስ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.