Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ህዝብና መንግስት ለመከላከያ ሰራዊት ከ85ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ህዝብና መንግስት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ለ4ኛ ዙር ከ85 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረገ።

ክልሉ እስከአሁን በአራት ዙሮች 295 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የአይነትና የገንዘብ መንግስት ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል።

1ሺህ 44 ሰንጋዎች፣ 986 በግና ፍየል እንዲሁም 20 መኪና ጭነት የተለያዩ ደረቅ ምግቦችና ሌሎች ቁሳቁስ በዛሬው እለት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አስረክቧል።

አጠቃላይ ድጋፉም ከ85 ሚሊየን 494 ሺህ ብር በላይ ግምት እንዳለው በርክክቡ ወቅት ተነግሯል ።

በደቡብ ክልል በአጠቃላይ እስከአሁን ባለው ሂደት በአራት ዙሮች በዓይነት የተደረገው ድጋፍ ከ255 ሚሊየን 928 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ሲሆን÷ በጥሬ ገንዘብ ደግሞ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተደርጓል።

ህዝቡ አሁንም ለሀገሩ ሉአላዊነት ደጀን ሆኖ እንዲቆም መጠየቁን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.