Fana: At a Speed of Life!

ወጣቱ መከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቱ በከፍተኛ ደረጃ መከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጥሪ አቀረቡ።

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ጉዳዮች መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን በስልጣን በቆየባቸው ዓመታት መከላከያ በአንድ ብሔር የበላይነት የተገነባ ነበር ብለዋል።

ኢትዮጵያን የማፍረስ አጀንዳ ይዘው ትግራይን የማልማት ሀሳብ በሚያቀነቅኑ ኀይሎች ይመራ ስለነበር መከላከያ ሠራዊትን የኢትዮጵያ ተቋም እንደሆነ አምኖ ለመቀበል አስቸጋሪ ነበርም ነው ያሉት።

ለዚህም ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በመከላከያ ሠራዊት ላይ የተፈጸመው ክህደትም የዚሁ ውጤት ማሳያ እንደሆነም ተናግረዋል።

ኮሎኔል ደመቀ የሠራዊቱን ቁመና የማስተካከል ሥራ ከተሠራ በኋላ ሀገራዊ ስሜት ያለው ተቋም እየሆነ መምጣቱን እያስተዋልን ነውም ብለዋል።

መከላከያ ሠራዊት በዚህ ጊዜ ከሌሎች የክልል እና የፌደራል የጸጥታ ተቋማት ጋር በመሆን አሸባሪውን የትህነግ ወራሪ ቡድን እስከመጨረሻው ለማጥፋት ትልቁን ድርሻ ወስዶ እየተፋለመ እንደሆነም ገልጸዋል።

መከላከያ ከሌለ እንደ ሕዝብም እንደ ሀገርም መቆም ስለማንችል በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወጣቱ በከፍተኛ ደረጃ መከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀል፣ እንዲሰለጥን፣ እንዲታጠቅ እና ተቋሙን እንዲያጠናክር እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።

በክልሉም ሆነ በዞኑ በልዩ ትኩረት እየተሠራበት መሆኑን በማንሳትም ወጣቱ በስፋት እየተመዘገበ እንደሆነ አመላክተው ወጣቱ አሁንም መከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀል ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.