Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያዊነት የኢትዮጵያውያን የመተሣሠሪያ ማንነት ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያዊነት የኢትዮጵያውያን የመተሣሠሪያ ማንነት መሆኑን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፉት ጽሁፍ፥ ኢትዮጵያዊነት ብዝኃነትን ማገሩ ያደረገና ጀግንነትን አጥሩ የሆነ መገለጫ ነው ብለዋል።
ከዚህ ባለፈም አንድነት ዓምዱ የሆነና ነጻነትን መንገዱ ያደረገ መለያ መሆኑን አውስተዋል።
አያይዘውም ኢትዮጵያዊነት ብዝኃ ባህል፣ ቋንቋ፣ እምነት እና አመለካከት ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን አንድ በማድረግ ለአንድ ሀገራዊ ዓላማ የሚያቆም ዕሴት መሆኑንም ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.