Fana: At a Speed of Life!

የደሴ ከተማ ወጣቶች እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች በወቅታዊ የህልውና ዘመቻ አጀንዳዎች የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ አስተባባሪ ዶክተር አለሙ ስሜ እንዲሁም የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል ተገኝተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፥ ወራሪው የትህነግ ሀይልን ለመቅበር ብሎም ለመላው ኢትዮጵያ ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ የዚህ ትውልድ ወጣት ታሪካዊ ሃላፊነተ አለበት ብለዋል።

ዶክተር አለሙ ስሜ በበኩላቸው፥ ወያኔን ብቻ ሳይሆን ተላላኪዎቹን ጭምር መቅበር ይጠበቅብናልም ነው ያሉት።

የሽብር ቡድኑ በደረሰባቸው አካባቢዎች ሁሉ የከፋውን የሽብር ጥቃት፣ የመብት ጥሰትና አሰቃቂ ወንጀል ፈፅሟል ያሉት የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ፥ በአማራ ህዝብ ላይ ሂሳብ አወራርዳለሁ ቢልም እየተደመሰሰ እና እየተቀጣ በመሆኑ እንኳን ደስ አለን ብለዋል።

የህልውና አደጋውን መመከት ለፍትሃዊነቱ ጥያቄ የለውም ያሉት አቶ አበበ፥ አባቶች ያስረከቡንን ሀገር ማስቀጠል ታሪካዊ ሃላፊነታችን በመሆኑ ትግላችን ይቀጥላል ሲሉም አስረድተዋል።

ለዚህም የደሴ ከተማ ወጣቶች እውነተኛ ኢትዮጵያዊነታችሁን በዚህ ታሪካዊ ጊዜ አሳዩ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን ሊቀመንበር ዶክተር በለጠ ሞላ ባስተላለፉት መልእክትም፥ አማራን ለማዋረድ ለመጣ ሃይል አንድ ሆነን መመከት ይጠበቅብናል ወጣቶችም መከላከያና ልዩ ሃይሉን በመቀላቀል ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል።

በመድረኩ የትህነግ ሃይል የህልውና አደጋነትና ምን መደረግ አለበት በሚሉ ጉዳዮች ላይ የጥናት ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በጋዜጠኞች ቡድን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.