Fana: At a Speed of Life!

የጋዳፊ ልጅ ከእስር ተለቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሶስተኛ ልጅ ሳአዲ ጋዳፊ ከ2014 ጀምሮ በሊቢያ ከታሰረበት የትሪፖሊ ማረሚያ ቤት መፈታቱ ተሰማ፡፡

ሳአዲ ጋዳፊ የሊቢያ ልዩ ኃይል አዛዥ ሆኖ አገልግሏል።

በፈረንጆቹ 2011 አባቱ ከስልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ወደ ኒጀር መኮብለሉ ይታወሳል፡፡

በወቅቱም በኒጀር በለስ ሳይቀናው ለሊቢያ ተላልፎ ከተሰጠ በኋላ በማረሚያ ቤት አሳልፏል።

አሁን ላይ ቀርቦበት ከነበረው ግድያን ጨምሮ ከተጠረጠረባቸው ወንጀሎች ነፃ መሆኑ በመረጋገጡ ከማረሚያ ቤት ተፈቷል።

ሳዓዲ ጋዳፊ ነጻ መባሉን ተከትሎ በግል ጀት ወደ ኢስታንቡል ማምራቱን ቢቢሲ አስነብቧል

የሊቢያ መንግስትም የልጁን መለቀቅ ለብሔራዊ እርቅ መንገድ ይከፍታል ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.