Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል በአማራ ክልል ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል በአማራ ክልል ለተፈናቃዮች የገንዘብ እና የዓይነት ድጋፍ ማድረጉን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ፡፡
 
ክልሉ የ10 ሚሊየን ብር፣ የሰንጋ፣ የደረቅ ምግብ እና የታሸገ ውሃ በባህርዳር በመገኘት ድጋፍ አድርጓል።
 
ድጋፉን የሲዳማ ከልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር አስረክበዋል።
 
ርዕሰ መስተዳድር ደስታ የኢትዮጵያን ታላቅነት ለማዋረድ የህወሓት የሽብር ቡድን እየሰራ ቢሆንም÷ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ እኩይ አላማው እንዳይሳካ እናደርገዋለን ብለዋል።
 
የሽብር ቡድኑ ከአማራ ልሂቃን ጋር የማወራርደው ሂሳብ አለኝ ማለቱም ፀቡ ልሂቃኑ ከሚወክሉት ህዝብ ጭምር መሆኑን ነው የገለፁት፡፡
 
ቡድኑ ጦርነቱን በአማራ ክልል ላይ ያድርገው እንጅ ጦርነቱ ከመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆኑ የሲዳማ ክልልም በቀጣይ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
 
ድጋፉን የተረከቡት ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር የሲዳማ ክልላዊ መንግሥትና ህዝብ በትግራይ ወራሪ ሃይል ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ለተደረገው ድጋፍ በክልሉ መንግስትና ህዝብ ስም ምስጋና ማቅረባቸውን ከማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.