Fana: At a Speed of Life!

የሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የሴካፋ ሻምፕዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታውን ዛሬ ያካሂዳል፡፡
መርሃ ግብሩ እንደሚያሳየው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግርኳስ ቡድን ከኡጋንዳው አቻው ሌዲ ዶቭስ ኤፍሲ ጋር ይጫወታል፡፡
በዚሁ መሠረት ከ10፡00 ሰዓት ጀምሮ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ያለፉትን ሦስት ጨዋታዎች 4 ለ2፣ 10ለ1 እንዲሁም 10ለ0 ማሸነፉን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.