Fana: At a Speed of Life!

በትምህርት ልማት ዘርፍ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ልማት ዘርፉ የኮሮና ቫይረስ ፣ የጸጥታ እና የፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ ሆኖ በርካታ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ፡፡

በዚህም የፖሊሲ ለውጦችን በማድረግ የቅድመ አንደኛ ደረጃ በሁለት ዓመት እንዲጠናቀቅ፣ መካከለኛ ደረጃ ከ 7ኛ እስከ 8ኛ ክፍል እና ሁለተኛ ደረጃ ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል እንዲሆን መደረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በግሉ ሴክተር የተያዘ እና በከተሞች ብቻ ትኩረት የተሰጠውን ዘርፍ ወደ መንግስት በማስገባት ባለፉት ሶስት ዓመታት በተሰራ ስራ 22 ሺህ ነባር 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ተጨማሪ ክፍሎችን በመገንባት 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ህጻናት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓልም ነው ያለው፡፡

በሌላ በኩል የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋትና ጥራቱን ለማሻሻል 1 ሺህ 74 አንደኛ ደረጃ ፣ 607 የሁለተኛ ደረጃ አዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እና ከ22 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ላይ የማስፋፊያ ስራዎች መሰራታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.