በምዕራብ ወለጋ ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ወለጋ፣ ነጆ ከተማ ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች ተይዘዋል።
ከዚህም ጋርተያይዞ ሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡
ተተኳሽ ጥይቶቹን የጫነው አይሱዙ መኪና ታርጋ ቁጥሩ AA 32684 ሲሆን÷ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው ሽንኩርት ጭኖ ጥይቶቹን በመሸፈን ከአዳማ ወደ ቤጊ ሲጓዝ በተደረገ ክትትል እንደሆነ በምዕራብ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የአካባቢ ጸጥታና ደህንነት ምክትል ዳይሬክተር ዋና ሳጅን ምትኩ ብርሃኑ ገልፀዋል፡፡
ምክትል ዳይሬክተሩ አያይዘውም እንደ ሁልጊዜው ሕብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ለፀጥታ አካላት እንዲያሳውቅ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡