Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ሚኒስቴር የኮቪድ19 ፕሮቶኮል አዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት አሰጣጡ እንዴት መሆን እንዳለበት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኮቪድ19 ፕሮቶኮል አዘጋጅቷል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በ2013ዓ.ም የትምህርት ዘመን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባስቀመጠው የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል መሰረት ትምህርት በቀንና ፈረቃ ሲሰጥ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት አሰጣጡ እንዴት መሆን እንዳለበት ደግሞ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኮቪድ19 ፕሮቶኮል አዘጋጅቷል።

በዚህም በ2014 ዓ.ም በሚኖረው የመደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ሂደት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንደሚካሄድ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.