Fana: At a Speed of Life!

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ምግብና ቁሳቁስ ከሰሜን ወሎ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉን የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገዝሙ ቀልቦ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና ለማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተት ዶክተር ጌታቸው ጉግሳ አስረክበዋል።

በተደረገው ጥሪ መሰረት ከተለያዩ ዩነቨርሲቲዎች እየመጣ ያለው ድጋፍ በከተማ አስተዳደሩ በኩል ለተፈናቃዮች እየተከፋፈለ መሆኑንም ዶክተር ጌታቸው ጉግሳ ገልፀዋል።

ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በርካታ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ወደ ነበሩበት እስከሚመለሱ ድረስ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ መቅረቡን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.