Fana: At a Speed of Life!

780 ኪሎ ግራም የሚመዝን ካናቢስ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ግምቱ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ መያዙን የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በኮሚሽኑ የሀዋሳ ቅርንጫፍ የሕግ ተገዢነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢዴሳ ለማ እንዳስታወቁት÷ አደንዛዥ ዕጹ የተያዘው ትናንት ሌሊት በጪጩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ነው።

ዕጹ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-A23897 አዲስ አበባ በሆነ ተሽከርካሪ ተጭኖ ከመሃል ሀገር ወደ ኬንያ ሲጓዝ መያዙንነው የገለጹት።

ክብደቱ 780 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ዕፅ÷ የዋጋ ግምቱ 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር እንደሚሆን አመልክተዋል።

አደንዛዥ ዕጹ በተሽከርካሪው በተጫነ ብሎኬት ሥር ተደብቆ ሊያልፍ ሲሞክር በፍተሻ ጣቢያው መያዙን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ቅርንጫፉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ ከ184 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው አደንዛዥ ዕፅ መያዙን ሥራ አስኪያጁ አክለው ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.