Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከጀርመን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከጀርመን አምባሳደር ቶማስ ተርሴገን ጋር ተወያዩ፡፡

በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ፣ መንግስት ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ እያደረገ ስላለው ጥረት እና በአንጻሩ የአሸባሪ ቡድኑ በአማራ ክልል እና በአፋር ክልሎች እያደረሰ ስላለው ጥፋት አምባሳደር ይበልጣል አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር አሁናዊ ሁኔታ እና በኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር ጉዳይ ዙሪያ ዛሬ ገለጻ መስጠታቸውን በሱዳን ከኢትዮያ ኢንባሲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.