Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ለሴካፋ የሴቶች ሻምፕዮንስ ሊግ ፍጻሜ አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ አስተናጋጅነት እየተካሄዳ ባለው የሴካፋ የሴቶች ሻምፕዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን የኡጋንዳ አቻውን በማሸነፍ ለፍጻሜ አልፏል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች መደበኛ 90 ደቂቃውን እና ተጨማሪ 30 ደቂቃውን 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ወደ መለያ ምት ለማምራት ተገደዋል፡፡
 
በተሰጠው የመለያ ምትም የንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የኡጋንዳው አቻውን ሌዲ ዶቭስ ኤፍሲን 5 ለ 4 በሆነ ድምር ውጤት በማሸነፍ ለፍጻሜ ጨዋታ ማለፉን አረጋግጧል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.