Fana: At a Speed of Life!

የአደጋ መንስኤዎችን በመለየት የትራፊክ ቁጥጥርና ክትትል ስርዓት ማሻሻያ ስልቶችን መተግበር ያስፈልጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማዋ ጠጥቶ ማሽከርከር፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር፣ የመቀመጫ ቀበቶ እና የግጭት መከላከያ ኮፊያ እንዲሁም ሌሎች ዋና ዋና የአደጋ መንስኤዎች ላይ እርምጃዎች በመወሰዳቸው በተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉ ተገለፀ፡፡
በአዲስ አበባ በየዕለቱ በአማካይ ከአንድ ሰው በላይ የሞት አደጋ የሚከሰት ሲሆን፥ ከሰባት ያላነሱት ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደሚደርስባቸው ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
በከተማዋ በትራፊክ ግጭት አደጋ በ2012 የተመዘገበው ሞት 448 ሲሆን÷ በ2013 የሞት መጠኑ ወደ 389 ዝቅ ብሏል ተብሏል፡፡
ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸርም 13 በመቶ የቀነሰ ሲሆን÷ በዚህም የ59 ሰዎችን ህይወት ከሞት መታደግ እንደተቻለ ነው የተነገረው፡፡
በትራፊክ ግጭት ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ዘንድሮ 1 ሺህ 824 ሲሆን÷ በ2012 1 ሺህ 847 መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖር ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
በዚህም 1 ነጥብ 25 በመቶ ወይም 23 ሰዎችን ከከባድ የአካል ጉዳት መታደግ ሲቻል÷ በአጠቃይ በ2013 1 ሺህ 824 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
በበጀት ዓመቱ የደረሰው የትራፊክ ግጭት አደጋ ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ በቁጥር 27 ሺህ 882 ፣ ከባድ የአካል ጉዳት 1 ሺህ 824፣ ቀላል የአካል ጉዳት 9 መቶ 94 እንዲሁም በሰው ላይ የደረሰ ሞት በቁጥር 389 አደጋዎች ተመዝግበዋል ነው የተባለው፡፡
የአደጋ መጠኖችን ለመቀነስ የአደጋ መንስኤዎችን በመለየት የትራፊክ ቁጥጥርና ክትትል ስርዓት ማሻሻያ ስልቶችን መተግበር ያስፈልጋልም ነው የተባለው፡፡
የአደጋ መጠኖችን ለመቀነስ የአደጋ መንስኤዎችን በመለየት የትራፊክ ቁጥጥርና ክትትል ስርዓት ማሻሻያ ስልቶችን መተግበር ያስፈልጋል የተባለ ሲሆን÷ ለዚህም ከሚዲያዎች ጋርተባብሮ መሥራት ይገባል ነው የተባለው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.