Fana: At a Speed of Life!

ከጳጉሜን እስከ ጳጉሜን እንደርሳለን በሚል መሪ ቃል ከ55 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ግንዛቤ ማስጨበጥ ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) “ከጳጉሜን እስከ ጳጉሜን እንደርሳለን” በሚል መሪ ቃል ከ55 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ግንዛቤ ማስጨበጥ መቻሉን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ባለፈው በጀት ዓመት 1 ሺህ 399 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ስራዎች ለማከናወን አቅዶ÷ 1 ሺህ 188 ኪሎ ሜትር በመገንባት የዕቅዱን 85በመቶ ማሳካት መቻሉን አስታውቋል።

በመንገድ ጥገና ሥራ 13ሺህ 604 ኪሎ ሜትር ለማከናወን ታቅዶ÷ 12 ሺህ 201 ኪሎ ሜትር በመጠገን 88 በመቶ መፈጸም መቻሉም ነው የተገለጸው፡፡

ለመንገድ ጥገና እና ለመንገድ ደህንነት እርምጃዎች ማስፈፀሚያ የሚሆን ከተለያዩ አገልግሎቶች 3ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ፥ 3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን መቶ በመቶ መፈጸም መቻሉን ገልጿል።

ለመንገድ ጥገና የሚውሉ 600 ሚሊየን የተገዙ ማሽኖች ለክልሎች መከፋፈሉንም ነው ያስታወቀው።

በአዲስ-አዳማ እና በድሬዳዋ-ደወሌ የማያቋርጥ የክፍያ መንገድ አገልግሎት 9 ነጥብ 3 ሚሊየን የተሽከርካሪ ፍሰት በማስተናገድ 375 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር መሰብሰቡንም ነው የገለጸው።

በዓመቱ በመንገድ ትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚደርሰውን የሰው ሞት በ10 ሺህ ተሽከርካሪ ከ34 ነጥብ 4 ወደ 32 ዝቅ ለማድረግ ታቅዶ ወደ 32 ነጥብ 6 ዝቅ ማድረግ ተችሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.