Fana: At a Speed of Life!

በማይጠብሪ በኩል ወረራ ለመፈጽም የሞከረው አሸባሪው ህወሓት እየተመታ ወደ መጣበት ተመልሷል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በማይጠብሪ በኩል ወደ አማራ ክልል ለመግባትና ወረራ ለመፈጸም የሞከረው የአሸባሪው ትህነግ ቡድን እየተመታ ወደ መጣበት መመለሱን የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያለአለም ፈንታሁን ተናግረዋል።
 
ዋና አስተዳዳሪው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ባለፉት ሶስት ቀናት የትግሉን አቅጣጫ የቀየሩ ድሎች ተገኝተዋል።
 
የጠላት ቡድን ወደ ክልሉ እንዳይገባ፤ ከገባም እንዳይወጣ አድርጎ መደምሰስን አላማ አድርገን ከሰራዊቱ ጋር በተደረገው ቅንጅታዊ ትግል ውጤት እየተገኘ ነው ብለዋል።
 
በጃናሞራ፣ በበየዳ፣ በጠለምት፣ በአዲአርቃይና በዳባት ወረዳዎች በርካታ ቁጥር ያለው የሚሊሻ አባላት 55 የሚሆኑ በሮችን ከሰራዊቱ ቀድሞ እንዲቆጣጠርና እንዲጠብቅ ተደርጓል ነው ያሉት።
 
በተለይም በአጅሬና ጃኖራ በኩል የተሰለፈው የጸጥታ መዋቅር ጠላት እንዳይገባ አድርጎ በመመከቱ አካባቢውን ከጥቃት መታደግ ችሏል ብለዋል።
 
ምንም እንኳን የሽብር ቡድኑን በማጥቃት እየመለስን ቢሆንም አሁንም ጠላት እርስ በርስ የመከፋፈል ተግባሩን እየገፋበት ስለሆነ ሁሉም ነቅቶ አካባቢውን ሊጠብቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።
 
በአሁኑ ሰአት ቦዛና አካባቢወ ከጠላት ወረራ ነፃ ሆኗል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው÷ ግንባር የሚገኘው የጸጥታ ሃይል ጠላትን እየተከታተለ ሌሎች አካባቢዎችንም አሰሳ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
የሽብር ቡድኑ ተመትቶ ሲመለስ እንደቆሰለ ጅብ ያገኘውን ሁሉ እያጠቃ ጉዳት እያደረሰ ቢሆንም÷ የአማራ ገበሬ ግን ከሚሊሻው ጋር ተቀናጅቶ እየታገለው ይገኛል ብለዋል።
 
በቀጣይም የአሁኑ ድል ሳያዘናጋን እስከመጨረሻው ልንፋለምና ይህንን አሸባሪ ቡድን ከኢትዮጵያ ልናስወግደው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
 
በሙሉጌታ ደሴ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.