Fana: At a Speed of Life!

በጉራጌ ዞን መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና የወሰዱ የሚሊሻ አባላት ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በጉራጌ ዞን መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ምልምል የሚሊሻ አባላት በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡
 
በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ÷ ሀገራችን ከጥንት ጀምሮ ነጻነቷን በማስጠበቅ እራሷን አስከብራ የቆየችና ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር መሆኗን አውስተዋል።
 
ክህደት በፈጸሙ ባንዳዎች የተቃጣብንን የጠላት ሴራ ለማክሸፍ መላው የሀገራችን ህዝብ ዳር እስከዳር በመነሳት አንድነቱን ማሳየቱንም አቶ አለማየሁ አብራርተዋል።
 
ባለፉት 27 ዓመታት የጥላቻና የመገፋፋት ፓለቲካ በፈጠረው ችግር ጥቂቶችን ብቻ ተጠቃሚ ያደረገ እንደነበር የተናገሩት ሃላፊው÷ይሁን እንጂ በመላው ህዝባችን ትግል ሀገራዊ ለውጥ እውን ሆኗል ነው ያሉት።
 
ይህ ለውጥ ያላስደሰተው አሸባሪው ህወሓት በህዝባችን ደም ለመነገድ የጥፋት አጀንዳ ቀርጾ ሀገር እያተራመሰ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
 
አሸባሪው ህወሓት እና ሸኔ በሀገራችን የሽብር ተግባር እየፈጸሙ መሆኑንም የገለጹት ሃላፊው÷ተመራቂ የሚሊሻ አባላት አካባቢያቸውን ብሎም ሀገራቸውን ለመጠበቅ ከፍተኛ ሃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ሀገራችን ነጻነቷን አስጠብቃ መቀጠል እንድትችል መላው የሀገራችን እና የክልሉ ህዝቦች በህልውና ዘመቻው ላይ እያደረጉት ያለውን ትግል እንዲያጠናክሩ ሃላፊው ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.