Fana: At a Speed of Life!

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ያለፈው በጀት ዓመት የበጎ አድራጎት ስራዎች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስቴር ባለፈው በጀት ዓመት የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ሰርቷል፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ከመተከል ተፈናቅለው በቻግኒ ከተማ ተጠልለው የነበሩ ዜጎችን በመጎብኘት የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጾ፥ ድጋፉ ለወገን አለኝታነትን ለማሳየት የተደረገ መሆኑንም ነው ያስታወቀው።

በተጨማሪም የትራንስፖርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ለትግራይ ክልል መንግስት ጊዜያዊ አስተዳደር ኮንስትራክሽን፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ወደ መደበኛው እንቅስቃሴ ለመመለስ እንዲያስችለው የ10 ሚሊየን ብር የገንዘብ እና የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ሚኒስቴሩ የህግ ማስከበር ዘመቻውን ለማገዝም የሚኒስቴሩ አመራርና ሰራተኞች “ደማችን ለመከላከያ ሠራዊታችን” በሚል መሪ ቃል ለመከላከያ ሰራዊት ደም የለገሱ ሲሆን÷ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የሚኒስቴሩ እና የአስሩ ተጠሪ ተቋማት አመራር እና ሰራተኞች ከደመወዛቸው ለመከላከያ ሰራዊት ከ57 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍም አድርገዋል።

ሚኒስቴሩ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሳተፈ ሲሆን÷ ቤት እድሳት ካስጀመረበት ቤቶች ውስጥ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ያስጀመራቸውን የቤቶች እድሳት አጠናቆ ለተጠቃሚዎች አስረክቧል፡፡

በቀጣይም በክረምት የቤት እድሳት ፕሮግራሙ የትራንስፖርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በማህበረሰብ አቀፍ የበጎ አድራጎት ስራዎች በመሳተፍ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን የመደገፍ ሥራ እንደሚቀጥል መግለጹ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.