Fana: At a Speed of Life!

አቶ ርስቱ በደቡብ ክልል የተሰሩ የልማት ስራዎች እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በክልሉ በበልግና መኸር የእርሻ ወቅቶች የተሰሩና እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

የዞኑ 30 በመቶ የሚሆነው የጤፍ ምርት የሚመረተው በሶዶ ወረዳ እንደሆነ የደቡብ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ ገልጸዋል፡፡

በአካባቢው የምርት እጥረት እንዳይገጥም ለማድረግ በሚያስችል መልኩ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

በበልግ የምርት ዘመን የምርት ቅናሽ ሊኖር እንደሚችል ታሳቢ ተደርጎም በ2013/14 ቀጣይ የእርሻ ወቅቶች ላይ ማካካሻ ለማድረግ በሚቻልባቸው ተጨማሪ ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

የምርት ሂደቱ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ የገለፁት ሃላፊው ÷ ከ75 በመቶ በላይ የሚሆነው መሬት በኩታ ገጠም እየለማ ይገኛልም ብለዋል፡፡

ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የዋጋ ንረትን ማስተካክል እንደሚቻልም ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡

ለዚህም በመስኖ ስንዴን ለማምረት መታቀዱን ነው ሃላፊው የገለጹት ፡፡

የመስክ ምልከታው ከጉራጌ ዞን በተጨማሪ በወላይታና ስልጤ ዞኖች በመዘዋወር የሚካሄዱ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የአካባቢው አርሶ አደሮች በበኩላቸው ÷ በአካባቢው የስንዴን ምርት በስፋት የሚመረት መሆኑን ገልጸው፣ በዘንድሮው የእርሻ ምርት ከአምናው የተሻለ ምርት ውጤት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.