Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ የፀጥታና የቁጥጥር ስራዎችን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የፀጥታና የቁጥጥር ስራዎችን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በጋራ ለመስራት የሚስችለውን  ስምምነት ተፈራርሟል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ፥በማአድን ዘርፍ ህግና ስርአትን ማስከበርና ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ስርአት ማስያዝ የቀጣዩ አመት እቅዳችን ስኬት ዋነኛው ግብአት ነው ሲሉ ገልጸዋል ።

በዛሬው እለትም ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን  የፀጥታና የቁጥጥር ስራዎችን በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል፣ስምምነቱም ከዛሬ ጀምሮ ወደ ተግባር የሚገባ ነው ብለዋል።

በስምምነቱ መሰረትም በድንበር አካባቢዎች ህገወጥ የወርቅ ዝውውር ለመከላከል ና ጠንካራ ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን፥ ወርቅ ወይም ሌሎች ማዕድናት በሚወጣባቸው አካባቢዎች ባሉ አዘዋዋሪዎች ላይ ጠንካራ ፍተሻ የሚደረግ ይሆናል ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም እነዚህ የጸጥታ ስራዎች በተደራጀና ወጥ በሆነ መልኩ መከናወን እንዲችሉ “የማአድን ፖሊስ ዲፓርትመንት” ይደራጃል ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.