Fana: At a Speed of Life!

ሀገር ከክብሯ ዝቅ እንዳትል፣ በነበረ ኩራቷ እንድትቀጥል ለማድረግ የተዘጋጃችሁ ውድ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ናችሁ  – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)”ሀገር ከክብሯ ዝቅ እንዳትል፣ በነበረ ኩራቷ እንድትቀጥል ለማድረግ የተዘጋጃችሁ ውድ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ናችሁ”  ሲሉ   ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

የብር ሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ34ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ምልምል መሠረታዊ ወታደሮች የፌዴራል እና የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች በተገኙበት ዛሬ አስመርቋል፡፡

በምርቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተመራቂዎችን “ሀገር ከክብሯ ዝቅ እንዳትል፣ በነበረ ኩራቷ እንድትቀጥል ለማድረግ የተዘጋጃችሁ ውድ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ናችሁ” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ሀገር ሁለት ዓይነት ሰዎችን ታበቅላለች ያሉት አቶ ደመቀ ሀገር የከዱ ባንዳዎች እና ስለሀገር ክብር ራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ እና የሚያሻግሩ ጀግኖች በየጊዜው ይፈጠራሉ፤ አሁን እያየን ያለነውም እርሱን ነው ብለዋል፡፡

“ከሁሉም የላቀ የሀገር ፍቅር መገለጫ የሆነውን የውትድርና ሙያ መርጣችሁ ስለተቀላቀላችሁ ልትኮሩ ይገባል” ነው ያሉት አቶ ደመቀ፡፡ ሀገር በእናንተ ጥረት ታፍራ እና ተከብራ ትዘልቃለች ብለዋል፡፡

አቶ ደመቀ ተመራቂዎቹ አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለማጥፋት ዘብ ከቆመው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ተቀናጅተው አዲስ ታሪክ እንደሚያስመዘግቡ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጀግና ከማህጸኗ በማይነጥፈው የኢትዮጵያ አብራክ ልዕልናችን ይቀጥላልም ብለዋል ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የምድር ኀይል ዋና አዛዥ ሌፍትናል ጀኔራል አሥራት ዴኔሮ፥ ኢትዮጵያ በታሪኳ የተፈተነችባቸውን ጊዜያት ሁሉ በድል አጠናቃለች ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጀግና ስለመሆኑ ጠላቶቻችን ያውቃሉ ያሉት ሌፍትናል ጀኔራል አስራት፥ በውጭም በውስጥም አኩሪ ገድሎችን ፈጽሟል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ የእናት ጡት ነካሾችን እስከወዲያኛው ለመሸኘት በአንድነት በቆመበት በዚህ ወቅት ክቡር የሆነውን የውትድርና ሙያ ስለተቀላቀላችሁ ኮርተናል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.