Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ አዳነች ማህበረሰቡን ዝቅ ብለው ለሚያገለግሉ ሰራተኞች ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጳጉሜ 02 የአገልጋይነት ክብር ቀን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማገልገል ክብር ነው! በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው ፡፡

ቀኑን ምክንያት በማድረግም ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተለይም ዘቅ ብለው ማህበረሰቡን በጽዳት የሚያገለግሉ ሰራተኞችን፣ የእሳት አደጋ ሰራተኞችን እንዲሁም የህዝብን ሰላም ለሚጠብቁ ፖሊሶች እና ደንብ አስከባሪዎችን ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ አገልጋይነት ክብር ነው፤ የምንኖርባትን ሀገር በታማኝነት እና በቅንነት ማገልገል ደግሞ የላቀ ክብር መሆኑን አውስተዋል፡፡

አዲስ ዓመትን ስንቀበል ከተማችንን እንዳጸዳን ሁሉ አዕምሯችን ውስጥ ያለውን የተዛባ አመለካከት አጽድተን በንጹህ ህሊና ማገልገል ይገባል ብለዋል፡

የከተማ አስተዳደሩ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለአዲስ አበባ እና ለፌዴራል ፖሊስ አባላት፣ ለእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ ለደንብ አስከባሪዎች እና ለፅዳት ሰራተኞች የሰንጋ፣ የዶሮ፣ የእንቁላል እና የዘይት ስጦታ አበርክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.