Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የአየር ንብረት ለውጥ እና የአካባቢ  ብክለትን ለመቋቋም ያላት ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው-ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር እና የአየር ንብረት ለውጥ እና የከባቢ አየር  ብክለትን ለመቋቋም ያላትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

ቻይና “ኢነርጂ ፣ የአየር ንብረት እና አካባቢ” በሚል መሪ ቃል የካርበን ልቀትን መቀነስ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ታይዩአን ኢነርጂ ዝቅተኛ የካርቦን ልማት ፎረም 2021ን አካሂዳለች ።

በዚህ ፎረም ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ  በቪዲዮ  ኮንፈረስ ተሳትፈዋል።

በወቅቱም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፉን በአካባቢ ጥበቃ ዘላቂ በሆነ መንገድ ለማልማት በትጋት እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2030 ሁለንተናዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማሳካት በሀገር አቀፍ ደረጃ አዲስ ፕሮግራም በመንደፍ እየሰራች መሆኑም አንስተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ አያይዘውም እንደዚህ አይነት መድረኮች መዘጋጀታቸው የካርቦን ልቀትን  በመቀነስ በቀጣይ  የተሻለ ከባቢ አየርን ለመፍጠር  ወሳኝ  ናቸው ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ  ቤጂንግ  ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር እና የአየር ንብረት ለውጥ እና የአካባቢ  ብክለትን ለመቋቋም ያላትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሀገሮች ፈጠራን በመጠቀም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቋቋም ቴክኖሎጂዎችን እና ምርጥ ልምዶችን እንዲቀበሉ የቻይና አጋርነት እና ድጋፍ  ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የቻይናው ጠቅላይ ሚንስትር ሊ ኬ ኪያንግ  በበኩላቸው ፥የቻይና መንግስት ከፍተኛ ጥራት ላለው ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአየር ብክለትን ለመከላከል ፣ የኃይል ድብልቅን እና የኢንዱስትሪ መዋቅርን በማሻሻል

ቻይና ሥነ -ምህዳራዊ እና የአካባቢን ጥራት ማሻሻል ችላለችም ነው ያሉት።

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ   የኮቪድ -19 ወረርሽኝ አሁንም በዓለም ዙሪያ እየተባባሰ መምጣቱን ተናግረዋል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ የዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ አለመረጋጋት  እየጨመረ በመምጣቱ ለዓለም አረንጓዴ እና ዘላቂ ልማት ከባድ ፈተናዎችን እያመጣ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። .

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ልማትና የአረንጓዴ ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ  የዓለም ሀገራት እጅ ለእጅ ተያይዘን   ለውጡ እና ማሻሻያው  ላይ  በቅርበት ልንሰራ  ይገባል ማለታቸውን በኢትዮጵያ  የቻይና ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.