Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ባለሃብቶች ለአፋር ክልል ተፈናቃዮች 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ባለሃብቶች በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የ100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ባለሃብቶቹ ያደረጉትን ድጋፍ ሠመራ ከተማ በመገኘት ዛሬ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ አስረክበዋል።

ከገንዘቡ ድጋፍ በተጨማሪም ባለሃብቶቹ በአፋር ግንባር ለሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት የበዓል መዋያ 400 በሬዎችን ድጋፍ አድርገዋል።

ድጋፉ አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል ባደረሰው ትንኮሳ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም እና

ጁንታውን ለመደምሰስ እየታገሉ ላሉ የአፋር ልዩ ሃይልና ሚሊሻ የሚውል መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

በርክክብ ስነ ስዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ አበባው ደስታ÷አባቶቻችን ያስረከቡንን ሀገር ማንም ሊያፈርሳት አይችልም፤ አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ ላይ የከፈተውን ጦርነት ለማክሸፍ የአፋር ህዝብ ትግል አድርጓል ብለዋል፡፡

አቶ ወርቁ አይተነው በበኩላቸው ÷አሸባሪው ህወሓት የጅቡቲን መስመር ለመቆጠጠር ያደረገውን ጥረት ለማክሸፍ የአፋር ህዝብ ያደረገውን ተጋድሎ አድንቀዋል፡፡

በውጊያ ጥበብ የአፋር ህዝብ ጁንታውን አንበርክኳል ያሉት ባለ ሃብቱ ÷ ከዚህ ህዝብ ጎን መቆም የሚያኮራ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም ባለሃብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በግላቸው 50 ሚሊየን ብር ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡

የባለሃብቱን ድጋፍ የተረከቡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ÷የአማራ ባለሃብቶች በዚህ ወቅት ከአፋር ህዝብ ጎን በመቆማቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የጁንታው ሃይል ኢትዮጵያን ለማፍረስ በአማራና በአፋር ህዝብ ላይ የከፈተው ጦርነት የጁንታውን ባህሪ በግልፅ ያሳየ መሆኑን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ሁሉም የሽብር ቡድኑን በጋራ እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.