Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በደረሰ የመኪና አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የዞኑ ፖሊስ የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ አደጋው የጭነት አይሱዙ ተሽከርካሪ ከጎሮ ሙጢ ወረዳ ድንችና ሰዎችን አንድ ላይ ጭኖ ወደ ሜታ ወረዳ ጨለንቆ ከተማ ሲጓዝ በመገልበጡ የደረሰ ነው፡፡

በአደጋው የ10 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በሰባት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም ለህክምና ወደ ድሬዳዋ መላካቸው ታውቋል፡፡

ጉዳቱን ያደረሰው አሽከርካሪ ለጊዜው ከአካባቢው መሰወሩ የተገለፀ ሲሆን ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ ገልጸዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.