Fana: At a Speed of Life!

አንጋፋው ድምፃዊ ዓለማየሁ እሸቴ ሀገሩን በቅንነት ያገለገለ ኢትዮጵያዊ ነው – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አንጋፋው ድምፃዊ ዓለማየሁ እሸቴ ሀገሩን በቅንነት ያገለገለና በታላቅ ፍቅር ዘመን ተሻጋሪ የሆኑ በርካታ የጥበብ ስራዎችን የሰራ ኢትዮጵያዊ ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡

ምክትል ከንቲባዋ የኢትዮጵያን ዘመናዊ ሙዚቃ አንድ ደረጃ ከፍ ያደረገዉን፣ ኢትዮጵያን ሳይሰስት ያገለገለውን፣ አንጋፋዉን የጥበብ ሰዉ አርቲስት አለማየሁ እሸቴን ዛሬ በክብር ተሰናብተነዋል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

ይህ የጥበብ ሰው በአካል ቢለየንም በስራዎቹ ከመቃብር በላይ እየታወሰ፣ እየተዘከረ እና እየተመሰገነ በልባችን ህያው ሆኖ ይኖራል ሲሉም ገልፀዋል።

“አዲስአበባ ቤቴ” የሚለው የብዙዎች የናፍቆት ማስታገሻ የሆነ የጥበብ ስራ፣ ተገቢዉን ክብር አግኝቶ እንዲታወስ በቀጣይ የምንሰራበት ይሆናል ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ።

ወይዘሮ አዳነች ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለሙያ አጋሮቹ እንዲሁም በሀገር ዉስጥና በመላው ዓለም ለሚገኙ አድናቂዎቹ በራሳቸውና በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርና ነዋሪዎች ስም መፅናናትን ተመኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.