Fana: At a Speed of Life!

አልማ በሰሜን ጎንደር ዞን በህወሓት ወራራ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ልማት ማህበር ህውሃት በከፈተው ጦርነት በሰሜን ጎንደር ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች ግምቱ 1 ሚሊየን ብር የሚሆን የፊኖ ዱቄት ድጋፍ አድርጓል።
ማህበሩ በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች አገልግሎት የሚውል 230 ኩንታል የፊኖ ዱቄት በደባርቅ ከተማ በመገኘት ለዞኑ አስተዳደር አስረክቧል።
 
የአልማ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ሞገስ÷ማህበሩ ከአሁን ቀደም በክልሉ ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች በመተከል፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ወሎና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ለተፈናቀሉ ዜጎች የተለያዩ ድጋፎች ማድረጉን አስታውሰዋል።
 
አሁንም በሰሜን ጎንደር ዞን በአሸባሪው ህወሓት የተፈናቀሉ ዜጎችን ችግር ለመጋራት በማሰብ ግምቱ 1 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 230 ኩንታል የፊኖ ዱቄት ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
 
የማህበሩ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መዝገበ አንዱዓለም በበኩላቸው÷ የተቋሙ ስራ ትኩረት የሚያደርገው ትምህርት ላይ ቢሆንም፣ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በዜጎች ላይ የህልውና አደጋ በመፍጠሩ ማህበሩ ትኩረቱን በወቅታዊ ድጋፍ ላይ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡
 
ማህበሩ በቀጣይ ለተፈናቃዮች የሚያደርገውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ም አስታውቋል።
 
በስንታየሁ አራጌ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.