Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደስታ ሌንዳሞ በመተከል ዞን ሰላም ለማስከበር የተሰማሩ ልዩ ሃይሎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌንዳሞ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ሰላም ለማስከበር የተሰማሩ የሲዳማ ልዩ ሃይል አባላትን ጎብኝተዋል፡፡
 
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ የኢትዮጵያን ትንሳኤ የማይፈልጉ ሃይሎች ክብሯን ለመንካት ሊሞክሩ ይችላሉ እንጅ በጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በክልል ልዩ ሃይሎች ጀብድ ጁንታው ተወግዶ ወደ ከፍታ ማማ እንወጣለን ብለዋል።
 
የሲዳማ ልዩ ሃይል ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚገኝበትን ቀጠና ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን የጁንታ ተላላኪ ሃይሎችን በማሳደድ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በመወጣት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
 
ሰላምን ለማስከበር የተሰማራውን የልዩ ሃይል አባላት ያሉበትን ሁኔታ የጎበኙት አቶ ደስታ÷ በሰሜን ግንባር እና በመተከል ዞን በአሸባሪው ህወሓት የተከፈተውን ጦርነት በጋራ በመመከት መጪውን አዲስ ዓመት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጋር በባህል፣ በልማትና በሰላም በጋራ እንደሚሰራም አውስተዋል።
 
የሲዳማ ክልል በመተከል ዞን ህግን ለማስከበር ለተሰማራው የሰራዊት አባላት 20 የሲዳማ ሰንጋ በሬዎች፣ለልዩ ሃይሉ አምቡላንስ እና ሌሎች ድጋፎችን ማበርከቱን ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን በበኩላቸው÷ በቀጠናው የተከሰተውን የጸጥታ ችግር መንግስት በውይይት ለመፍታት ጥረት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ይሁን እንጂ የሽፍታው ቡድን ግድያን በመምረጡ አሁን ላይ ሰራዊቱ እየወሰደ ያለውን እርምጃ የክልሉ መንግስት እንደሚደግፍ ገልጸዋል።
 
ከአሁን በፊት ቀጠናውን የህወሓት ቡድን ለልማት በሚል ሴራ ለግጭትና ሁከት ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ሃይሎችን ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የክልሉ የጸጥታ አካላት ከሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ከሲዳማ ክልል ልዩ ሃይሎች እና ከሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ጋር እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.